ቀጥታ፡

"ስነ ምግባራዊ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2017(ኢዜአ)፡-"ስነ ምግባራዊ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

መድረኩ የአዲስ አበባ የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው።


 

በመድረኩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ(ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ፣ የአዲስ አበባ የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ እና ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

መድረኩ ከሙስና የጸዳ ከተማ እና ሀገር ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ውስጥ ህብረተሰቡ አጋዥ እንዲሆን የጋራ አረዳድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም