ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 27/2017(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በቁልፍ የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር አላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው በልምምድ ልውውጥ፣ በስልጠና መርሃ ግብሮች፣ የብክለት አስተዳደር፣ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር፣ የስነ ምህዳር ጥበቃ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ጠንካራ የከባቢ አየር ሪፎርም ኢኒሺቲቮችን በጋራ በመተግበር ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከሩሲያ መንግስት አቻ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያን እና የምርምር ተቋማት ጋር ትስስር እንዲፈጥር በማድረግ ትብብሩን ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሰራ ገልጸዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በአጋርነትና ኢኖቬሽን አማካኝነት ዘላቂ የከባቢ አየር መፍትሔዎችን ለማምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም