አዲስ አበባ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አንደበት - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አንደበት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የማጠቃለያ መርሃ ግብር አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተሳተፉ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች የባህላዊ ሙዚቃ ትርኢት አሳይተዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የበዓሉ ተሳታፊዎችም አዲስ አበባ የሁሉም ቤትና የጋራ መናገሻ እንዲሁም የውበት መገለጫ ተምሳሌት መሆኗን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች፣ ሁሉን ያማከሉ፣ የአብሮነት ማሳያና የጋራ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በየአመቱ ህዳር 29 የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ባህላቸውን ለማስተዋወቅ፣ አንድነትን ለማጠናከር፣ በልዩነት ውስጥ ውበትን ለማድመቅ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያን በልዩነት ውስጥ አንድነትን በማጠናከር ለሀገራቸው ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል።