በአርባ ምንጭ ከተማ ከ122 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጋሞ አደባባይ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
በአርባ ምንጭ ከተማ ከ122 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጋሞ አደባባይ ተመረቀ
አርባ ምንጭ፤ ህዳር 26/2017(ኢዜአ)፡- በአርባ ምንጭ ከተማ ከ122 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጋሞ አደባባይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተመረቀ።
በአደባባዩ የምረቃ ሥነስርአት ላይ ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።
አደባባዩ የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው የጋሞ ህዝብ መገለጫ እንደሆነም በምረቃው ላይ ተገልጿል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዳሙ ሻምቤል ለኢዜአ እንደገለጹት አደባባዩ በ122 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ነው።
ለየት ባለ መልኩ ተገንብቶ ዛሬ ማምሻውን የተመረቀው አደባባይ በከተማዋ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ላለው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ሌላኛው ድምቀት ሆኗል ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አደባባዩን የመረቁ ሲሆን ሌሎች የፌዴራል፣ የክልል፣ የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችም በምረቃው ላይ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል።