19ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል አዲስ አበባችን የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ተምሳሌት መሆኗን በሚመጥን ልክ ተከብሯል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2017(ኢዜአ)፦ ዛሬ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በአድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካንዚም አዳራሽ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ባማረና በደመቀ ሁኔታ አክብረናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በዓሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ቤት፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ መናገሻ፣ የአፍሪካ ህብረት መዲና እና ሶስተኛዋ የዓለም ዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ የህብረብሄራዊ አንድነታችን ተምሳሌት መሆኗን በሚመጥን ልክ ተከብሯል ብለዋል።

በበዓሉ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና የሁሉም ክልሎች አፈ ጉባኤዎች መገኘታቸውንም አመላክተዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም