19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የማጠቃለያ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የማጠቃለያ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መርኃ-ግብር በፓናል ውይይትና በባህል ፌስቲቫል እያከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ቡዜና አልከድር፣ የክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባዔዎችና የጸጥታ ተቋማት አባላትና ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የብሔር፤ ብሔረሰቦች ተወካዮች ባህላቸውን የሚያሳይ የሙዚቃ ትርዒት አቅርበዋል።
ከተማ አስተዳደሩ 19ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን "ሃገራዊ መግባባት ለብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች ሲያከብር የቆየ ሲሆን በዛሬው እለት የማጠቃለያ መርኃ-ግብሩን እያካሔደ ይገኛል።