ቀጥታ፡

በደሴ ከተማ በ116 ሚሊዮን ብር የገበያ ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

ደሴ፣ህዳር 26/2017( ኢዜአ )፡- በደሴ ከተማ አስተዳደር በ116 ሚሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ተጀመረ።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም መሀመድ (ዶ/ር)፣ የደሴ ከተማን የኮሪደር ልማት እንዲደግፉ የተመደቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሩ አመራር አባላትና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ እንደገለፁት፤ ማዕከሉ በ3 ሺህ 500 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው።

ማዕከሉ ዘመናዊ ሼዶችን ያካተተ ሲሆን የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች በስፋት የሚቀርቡበት መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ ከማገናኘት ባለፈ የጅምላ አከፋፋዮችም ምርታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ በ116 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን ግንባታውን በአራት ወራት ውስጥ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቃ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክተዋል።

 
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም