ቀጥታ፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች አቦሎ የተሰኘውን የተርኪዬ የግብርና ማሽኖች አምራች ኩባንያ ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ አቦሎ በተሰኘው የተርኪዬ የግብርና ማሽኖች አምራች ኩባንያ ጉብኝት አድርገዋል።

የከፍተኛ አመራሮቹ ልዑክን እና የኩባንያው የስራ ኃላፊዎች በትብብር ሊሰሩ በሚችሉባቸው መስኮች ላይ ተወያይተዋል።

ተቋማቱ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በተርኪዬ ኮንያ ከተማ የሚገኘው አቦሎ የግብርና ማሽኖች አምራች ኩባንያ የተቋቋመው እ.አ.አ በ1975 ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም