ለቀድሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ ሽኝት ተደረገላቸው - ኢዜአ አማርኛ
ለቀድሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ ሽኝት ተደረገላቸው
አዲስ አበባ፤ ህዳር 24/2017(ኢዜአ):- የቀድሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር በመሆን መሾማቸውን ተከትሎ በባለሥልጣኑ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
አቶ መሐመድ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት በመሩበት ወቅት ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ለውጦችን እንዲያስመዘግብ መስራታቸው ተገልጿል።
የባለሥልጣኑ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች አቶ መሐመድ በአመራር ብቃትና ተቋሙ ላይ የሚታዩ ለውጦች እንዲመዘገቡ በማድረግ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነው፤ በተሾሙበት መስሪያ ቤት መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
አቶ መሐመድ እድሪስ ከሶስት ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል።
ሽኝት የተደረገላቸው አቶ መሐመድ እድሪስ፣ ተቋሙ ያስመዘገበው ለውጥ የሁሉም የጋራ ስራ መሆኑን በመግለጽ፤ በቀጣይም ከቀድሞ ተቋማቸው ጋር ስራዎችን በትብብር እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።