ቀጥታ፡

አቶ ገበያው ታከለ የአፍሪካ ጅምናስቲክ ፌዴሬሸን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 24/2017(ኢዜአ):- አቶ ገበያው ታከለ የአፍሪካ ጅምናስቲክ ፌዴሬሸን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ።

ፌዴሬሽኑ በግብጽ ጠቅላላ ጉባዔውን አድርጓል።

በጉባኤው አቶ ገበያው ታከለ ለቀጣይ አራት ዓመታት የአፍሪካን ጅምናስቲክ ፌዴሬሸን ከሰባቱ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች መካከል አንዱ ሆነው እንዲያገለግሉ በከፍተኛ ድምጽ መርጧል። 

አቶ ገበያው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸው ኢትዮጵያ በአህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚኖራት የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

አቶ ገበያው በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በኳታር ዶሀ በተካሄደው በ85ተኛው የዓለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ካውንስል (FIG Council) አባል ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ የጅምናስቲክስ ስፖርት ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት አቶ ገበያው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሜቴ የክብር አባል መሆናቸውን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም