የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በወላይታ ሶዶ ያስገነባውን ስቱዲዮ አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በወላይታ ሶዶ ያስገነባውን ስቱዲዮ አስመረቀ
ሶዶ፤ ህዳር 24/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ ያስገነባውን ስቱዲዮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ አስመርቋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል