ቀጥታ፡

19ኛው የብሔር፤ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዱባይ ተከበረ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 24/2017(ኢዜአ):-19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲና በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት በጋራ ተከብሯል።

በአከባበሩ ላይ የሁለቱ ሚሲዮን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።


 

በዓሉ ኢትዮጵያ የብዝኃነት ተምሳሌት መሆኗን ለሌላው ለማስተዋወቅ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገልጿል።

በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች እና አልባሳት ለእይታ መቅረባቸውን በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

19ኛው የብሔር፤ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በአርባምንጭ ከተማ ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም