ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ የሆኑት አቶ ፍሬዘር በቀለ ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50,000 የአሜሪካ ዶላር በታማኝነት ለመንገደኛው አስረከቡ

አዲስ አበባ፤ህዳር 23/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16 ቀን 2024 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50,000 የአሜሪካ ዶላር በታማኝንት ለመንገደኛው ማስረከባቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ።

የአየር መንገዱ እንደገለጸው፥ ባልደረባው በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠር በገባው ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምግባር አክብሯል።

አቶ ፍሬዘር ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት ማስመስከራቸውን አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ለማሳደግ  ምንግዜም ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም