ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የቺካጎ ኮንቬንሽን የተፈረመበት ቀን መታሰቢያ በተለያዩ ሁነቶች ሊያከብር ነው

አዲስ አበባ፤ህዳር 23/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንና 80ኛው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪየሽን ድርጅት የምስረታ በዓላትና የቺካጎ ኮንቬንሽን የተፈረመበት ቀን መታሰቢያ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበሩ ተገለጸ።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ እና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጌታቸው መንግስቴ ሁነቶችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዝሃን በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ሁነቶችን አስመልክቶ በአቪዬሽን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኤግዚቢቪሽን፣ ሲምፖዚየም እና ፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

ሕብረተሰቡም በሁነቶቹ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።


 

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው መንግስቴ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ሴክተር ለኢትዮጵያ ባህል፣ ቱሪዝም፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን መግለጻቸውን ከትራንስፖርትና ሎጅቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም