የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሲዳማ ክልል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሲዳማ ክልል እየተከበረ ነው
ሀዋሳ፤ ህዳር 23/2017 (ኢዜአ):-19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሲዳማ ክልል እየተከበረ ነው።
በዓሉ በሲዳማ ክልል ደረጃ ዛሬ እየተከበረ ያለው "ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
በዓሉ ቀደም ሲል በክልሉ ከቀበሌ ጀምሮ በተለያዩ መርሀግብሮች ሲከበር መቆየቱ ተመላክቷል።
ዛሬ በክልል ደረጃ እየተከበረ ያለው በዓል የማጠቃለያ ሲሆን በበዓሉ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በዓሉ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት እንዲከበር አስተዋጾ ላደረጉ አካላትም ከክልሉ ምክር ቤት ዕውቅና ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር እንደሚኖር ተገልጿል።