ቀጥታ፡

አትሌት መገርቱ አለሙ የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ፤ህዳር 22/2017(ኢዜአ)፦ዛሬ ረፋዱን በተካሄደው የቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር የአሸናፊነት ቅድመ ግምት አግኝታ የነበረችው አትሌት መገርቱ አለሙ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ የውድድሩን ርቀት ለማጠናቀቅ 2ሰዓት ከ16 ደቂቃ፤49 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።

ሌላዋ በውድደር የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩዬ መስፍን ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ዩጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንድ ደግሞ የሁለተኝነቱን ደረጃ ወስዳለች።

ባለፈው አመት በተካሄደው የቫሌንሲያ ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት ማጠናቀቃቸው አይዘነጋም።

በወቅቱ አትሌት ወርቅሽ ደገፋ በቀዳሚነት ስትገባ ሌላኛዋ የኢትዮጵያ አትሌት አልማዝ አያና ሁለተኛ አትሌት ህይወት ገብረኪዳን ሶስተኛ በመግባት አሸንፈዋል።

የቫሌንሲያ ማራቶን የሴቶች ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት አማኔ በሪሶ ስትሆን ከሁለት አመት በፊት በተካሄደው ውድድር ርቀቱን በ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባ ማሸነፏ ይታወሳል።

አትሌቷ በዘንድሮው የቫሌንሲያ ማራቶን ላይ በጉዳት ምክንያት እንደማትሳተፍ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም