19ኛው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
19ኛው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተከበረ ነው
ሚዛን አማን፤ህዳር 22/2017 (ኢዜአ):-19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት፤ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እየተከበረ ነው።
በዓሉ ከቀበሌ ጀምሮ በሁሉም ዞኖች የተከበረ ሲሆን ዛሬ እንደ ክልል የማጠቃለያ መርሃ ግብር በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የሁሉም ብሔረሰቦች ተወካዮች፣ የዞኖችና እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቀኑን በአንድነት በማክበር ላይ ናቸው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 13 ብሔረሰቦች ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ተዋደውና ተከባብረው በአንድነት የሚኖሩበት ክልል ነው።