ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ባህል ልዑክ በሩሲያ ካዛን ከተማ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በዓለም አደባባይ አስተዋወቀ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ባህል ልዑክ በሩሲያ ካዛን ከተማ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ በመገኘት ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን በዓለም አደባባይ አስተዋውቋል።

የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ መሪዎች እና ሙሉዓለም የባሕል ማዕከል የባህል ቡድን በሩሲያ ካዛን ከተማ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው መገኘታቸው ይታወሳል።

ወደ ስፍራው ያቀናው የሙሉዓለም የባሕል ማዕከል ልዑክ በዓለም አቀፉ መድረክ ላይ የተለያዩ ባህልና ኪነ ጥበብ ሥራዎቹን ለተመልካች አቅርቧል።

ቡድኑ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትንም በዓለም አደባባይ ሲያስተዋውቁ አምሽተዋል።

ልዑኩ ባቀረባቸው ሥራዎች አድናቆት እና ምስጋና ተችሮታል።

ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ የተደረገበት መድረክ እንደነበረም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም