ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ ሲደርስ በሃገሪቱ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ናዩማ ቦካይ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፤ህዳር 22/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ ዳግም በጀመረው የመንገደኞች በረራ ሞንሮቪያ ሲደርስ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ናዩማ ቦካይ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በዚህም ወቅት፥በኢትዮጵያ እና በላይቤሪያ መካከል የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በመጀመር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ብሎም አፍሪካን እርስ በርስና ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት እየተጫወተ ያለውን የመሪነት ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም