ቀጥታ፡

የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2017(ኢዜአ):- በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን የተመራ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ የአየር መንገዱ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የልዑካን ቡድኑ ከውይይቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ አየር መንገዱ በአፍሪካ አህጉር በመሪነት የሚጠቀስባቸውንና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ያስጠበቀባቸውን የስራ ክፍሎችና የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎችን ተዘዋውሮ መመልከቱን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መወያየታቸው ይታወቃል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ እና ባንኩ መካከል ሊኖር ስለሚችለው የአረንጓዴ ኢነርጂ፣ አቪዬሽን እና መሠረተ ልማት ትብብር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ጂን ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ኢ/ር ዶ/ር) እና ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም