ፋሲል ከነማ በሊጉ ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ - ኢዜአ አማርኛ
ፋሲል ከነማ በሊጉ ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአማካይ ተጫዋቹ በረከት ግዛው በ49ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጋለች።
ውጤቱን ተከትሎ በመጀመሪያ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካሸነፈበት ጨዋታ ወዲህ ከድል ርቆ የነበረው ፋሲል ከነማ ከሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ተመልሷል።
በውድድር ዓመቱም ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
ፋሲል ከነማ በ10 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል።
በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በ13 ነጥብ በነበረበት ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ከምሽቱ 1 ሰዓት መቀሌ 70 እንደርታ ከባህር ዳር ከተማ ይጫወታሉ።