ቀጥታ፡

በህብር ላይ የተመሰረተ አንድነትና ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር የሃገራችንን ብልፅግናና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ይኖርብናል - አምባሳደር ተፈራ ደርበው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2017(ኢዜአ)፦በህብር ላይ የተመሰረተ አንድነትና ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር የሃገራችንን ብልፅግናና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ገለጹ።

19ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ቤጂንግ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሚስዮን ተከብሯል።


 

ዘንድሮ "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ቻይና የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት እና የሚስዮኑ ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሚስዮኑ መሪ ባለ ሙሉስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው በህብር ላይ የተመሰረተ አንድነትና ሀገራዊ መግባባት በመፍጠር የሃገራችንን ብልፅግና እና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።

ለበዓሉ በተዘጋጀው የመወያያ ሰነድ መነሻነትም ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የምንፈልገውን ልማትና ብልፅግና ለማረጋገጥ እንዲሁም በቂ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር እኩልነትና ፍትሓዊነትን የተመረኮዘ ስርዓት መዘርጋት ለነገ የማይባል የቤት ስራ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ምሁራን የሃገራችንን ባህል እና እሴት እንዲሁም ሕብረተሰባዊ ትስስር መሰረት ያደረጉ አስተሳሰቦችን በማስረፅ ህብረ ብሄራዊ አንድነት እና መግባባት ለመፍጠር የላቀ ድርሻ እንዳላቸው መመላከቱ ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም