በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየጎበኙ ነው
ሐረር፤ ህዳር 21/2017 (ኢዜአ)፡-በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መሀመድ አብዱረሃማን የሚመራ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየተመለከቱ ነው።
በጉብኝቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መሀመድ አብዱረሃማን እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የክልሉ የካቢኔ አባላትና የዘርፍ መስሪያ ቤት ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በዚህም መሰረት በከተማው በመጀመርያው ምዕራፍ በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ስራዎች የክልሉ ኮንስትራክሽን እና መሰረተ ልማት ስራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፈቲህ ረመዳን ቀርቧል።
በቅርስና ቱሪዝም፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታና ጥገና፣ በአረንጓዴና መናፈሻ ልማት እንዲሁም በተቀናጀና ተናባቢ የትራንስፖርት ልማት የተከናወኑ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።
የኮሪደር ልማት ስራዎችም ለነዋሪው እና ለጎብኚው ምቹ፣ ሳቢና ማራኪ ገጽታን ከመፍጠር ባለፈ ሐረርን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻነቷን እያጎለበተ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።