ቀጥታ፡

የፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን-ኖኤል ባሮት ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2017(ኢዜአ):- የፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን-ኖኤል ባሮት በኢትዮጵያ የብሔራዊ ሙዚየምንና የሊሴ ገብረ ማሪያም ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።


 

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በዚሁ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የረዥም ዘመን ታሪክ ያላትና የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት መሆኗን አስታውሰዋል።

የፈረንሳይ መንግስት በተለያዩ ጊዜ ወደ ሀገሪቱ የገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች እንዲመለስ ማድረጉ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ብለዋል።

የፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን-ኖኤል ባሮት በበኩላቸው ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1960ዎቹ ከመልካ ቁንጥሬ መካነ ቅርስ ለምርምር ወደ ፈረንሳይ ሀገር ተወስደው የነበሩ ጥንታዊ የሰው ዘር የተገለገለባቸውን የድንጋይ መሣሪያዎች ለቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ማስረከባቸው ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም