ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞንሮቪያ የሚያደርገውን በረራ ዳግም አስጀመረ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የላይቤሪያ ዋና ከተማ   ሞንሮቪያ በረራ ዳግም ዛሬ አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣በኢትዮጵያ የላይቤሪያ አምባሳደርና ሌሎች የአየር መንገዱ የስራ ሃፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል።


 

አየር መንገዱ በ2020 ላይ አቋርጦት የነበረውን በረራ ነው እንደገና ዛሬ ያስጀመረው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ወደ ላይቤሪያ በረራ መጀመሩ የምጣኔ ሀብት፣ የቱሪዝምና ንግድ፣ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የA350 -1000 አውሮፕላን ከኤር ባስ ኩባንያ መረከቡ ይታወሳል።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት ባሉት 147 አውሮፕላኖች 140 ዓለም አቀፍና 22 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን የሚሸፍን ሲሆን እ.አ.አ በ2035 ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር በማሳደግ በዓመት 67 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማጓጓዝ ራዕይ ሰንቆ እየሰራም ይገኛል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም