መቻል የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ድል አስመዝግቧል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል የሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ድል አስመዝግቧል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአማካይ መስመር ተሰላፊው ሽመልስ በቀለ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አብዱልከሪም ወርቁ ቀሪዋን ጎል ለመቻል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አሕመድ ሁሴን የአርባምንጭ ከተማን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ17 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ ከነበረበት 9ኛ ደረጃ ወደ 11ኛ ዝቅ ብሏል።
መቻል በ10ኛ ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል።