አዳማ ከተማ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል በኢትዮጵያ ቡና ላይ አስመዝግቧል - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል በኢትዮጵያ ቡና ላይ አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2017 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አጥቂው ስንታየሁ መንግስቱ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የፊት መስመር ተሰላፊው አንተነህ ተፈራ ኢትዮጵያ ቡናን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አስቆጥሯል።
አዳማ ከተማ በሊጉ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን አግኝቷል። ቡድኑ በ11 ነጥብ ከነበረበት 14ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ከፍ ብሏል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በስምንት ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከሊጉ መሪ መቻል ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።