የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የማጠቃለያ መረሃ ግብር በሠመራ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የማጠቃለያ መረሃ ግብር በሠመራ እየተካሄደ ነው
ሠመራ፤ ህዳር 20/2017(ኢዜአ)፡- 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የማጠቃለያ መረሃ ግብር በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ እየተካሄደ ነው ።
"አገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት "በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተከበረ ያለው።
በዚሁ የማጠቃለያ መረሃ ግብር ላይ የኦሮሚያ ፣ አማራ፣ ሶማሌ ፣ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አፈ ጉባዔዎች፣ የመከላከያ መኮንኖችና አባላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በአሁኑ ወቅት የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ አሲያ ከማል የአፋር ቱባ ባህላዊ እሴቶችን እያስተዋወቁ ነው።