በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 10 ሰአት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በአሰልጣኝ አብዱ ቡሊ የሚመራው አዳማ ከተማ በሊጉ እስከ አሁን ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ ሶስት ጊዜ ሽንፈት ገጥሞታል። ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቷል።

ሰባት ግቦችን ሲያስቆጥር ዘጠኝ ጎሎችን አስተናግዷል። አዳማ ከተማ በስምንት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ  ባከናወናቸው ሰባት ጨዋታዎች ሁለት ሲያሸንፍ በሶስቱ ተሸንፏል። ሁለት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል።

በጨዋታዎቹ ቡድኑ ሰባት ግቦችን ሲያስቆጥር በተመሳሳይ ሰባት ጎሎችን አስተናግዷል። 

በነጻነት ክብሬ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና በስምንት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከሊጉ መሪ መቻል ይጫወታሉ።

አርባምንጭ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች ሶስት ጊዜ ሲያሸንፍ በተመሳሳይ ሶስት ጊዜ ተሸንፏል። አንድ ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። 

በጨዋታዎቹ ስድስት ግቦችን ሲያስቆጥር በተመሳሳይ ስድስት ጎሎች ተቆጥሮበታል።

በበረከት ደሙ የሚመራው አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው መቻል በሊጉ ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች አራት ጊዜ ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። ሁለት ጊዜ አቻ ተለያይቷል።

ቡድኑ በጨዋታዎቹ 12 ግቦችን ሲያስቆጥር አምስት ጎሎችን አስተናግዷል።

በገብረክርስቶስ ቢራራ የሚሰለጥነው መቻል በ14 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የዘጠነኛ  ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ ሲለያዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም