በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2017 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለ ምንም አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ14 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ከፍ ብሏል።
ድሬዳዋ ከተማ በ12 ነጥብ በነበረበት ሰባተኛ ደረጃ ላይ ረግቷል።
ቀን ላይ በተደረገ የዘጠነኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ መድን አንድ አቻ ተለያይተዋል።