የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "የተከበረች ሀገር የማይበገር አየር ኃይል" በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
የበዓሉ አካል የሆነ የዋዜማ ዝግጅት ቢሾፍቱ በሚገኘው የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ እየተካሄደ ነው።
በዝግጅቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የመከላከያ ከፍተኛ ጦር መኮንኖች፣ የአፍሪካ ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች የሌሎች የፀጥታ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አየር ኃይልን ወደ ከፍታ ለመውሰድ በሚደረጉ ጥረቶች የተለያዩ ተሳትፎ ያደረጉ እና የደገፉ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ተቋማት ዕውቅና እና ምስጋና አሰጣጥ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።