ህብረተሰቡ ከባንክ የተደወለ አስመስለው የግለሰቦችን የባንክ ምስጢር ቁጥር በመቀበል ከሚያጭበረብሩ ወንጀለኞች እንዲጠነቀቅ ፖሊስ አሳሰበ - ኢዜአ አማርኛ
ህብረተሰቡ ከባንክ የተደወለ አስመስለው የግለሰቦችን የባንክ ምስጢር ቁጥር በመቀበል ከሚያጭበረብሩ ወንጀለኞች እንዲጠነቀቅ ፖሊስ አሳሰበ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2017(ኢዜአ)፦ ህብረተሰቡ ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው የተለያዩ ስልኮችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ ምስጢር ቁጥር በመቀበል ገንዘብ ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች ሊጠነቀቅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳሰበ፡፡
ፖሊስ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተለያዩ የባንክ ስሞችን በመጠቀም ለግለሰቦች በመደወል የባንክ አካውንቱን በመናገር ሲስተም እያስተካከልን ነው፤ የባንካችን ተሸላሚ ደንበኛ በመሆንዎ ‘እንኳን ደስ አለዎት’ በማለት እና የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም የሞባይል ባንኪንግ ኮድ እንዲያስገቡ በማግባባት በአካውንት የተቀመጠ ገንዘብን ወደራሳቸው የሚወስዱ አጭበርባሪዎች መበራከታቸውን ደረሼበታለሁ ብሏል፡፡
ሕብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የመጭበርበር ወንጀል እራሱን በመጠበቅ ከዚህ በታች በስምና በፎቶ ግራፍ የተገለጹትን ተጠርጣሪዎች ሲመለከት ተቋሙ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡