ባህር ዳር ከተማ ስሑል ሽሬን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ከተማ ስሑል ሽሬን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ስሑል ሽሬን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አጥቂው ወንደሰን በለጠ በ46ኛው እና በ84ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በ13 ነጥብ ከነበረበት ዘጠነኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ ከፍ ብሏል። በውድድር ዓመቱም አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ስሑል ሽሬ በሰባት ነጥብ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 16ኛ ዝቅ ብሎ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሕዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።