ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት አላት- አምባሳደር ፍቃዱ በየነ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ገለጹ።

አምባሳደር ፍቃዱ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን አቅርበዋል።

በዚሁ ወቅት አምባሳደሩ ከፕሬዝዳንቷ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ አዲስ የተሾሙት አምባሳደር በኢትዮጵያና በታንዛኒያ መካከል የቆየ ታሪካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መኖሩን አንስተው ትብብሩ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስኮችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም