ቀጥታ፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ተበርክቶላቸዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሳልቫኪር ማያርዲት ለኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳልን አበርክተውላቸዋል፡፡

የተበረከተላቸው የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የሁለቱን ሀገራት የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከር፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ሪፎርም ሂደትን በመደገፍ የአገልግሎቱን ከፍተኛ መኮንኖች አቅም ለመገንባት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰጡት የትምህርትና ስልጠና እድሎች አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል፡፡


 

በሥነ-ሥርዓቱም የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ቾል ማውትን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሀዲ እና የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል አተም ማሮል መገኘታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም