ቀጥታ፡

ሶስተኛው የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ህዳር 14/2017(ኢዜአ)፦ ሶስተኛው የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።

በኤክስፖው መክፈቻ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ሚኒስትሮች የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ ኤክስፖውን መርቀው ከፍተዋል።

ኤክስፖው የኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቶች ለዓለም ማስተዋወቅና ለኢኮኖሚና ለውጭ ምንዛሬው ያለውን አበርክቶ ማሳደግን ዓላማው አድርጓል።

በኤክስፖው በርካታ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ኤክስፖው ሀገር በቀል ድርጅቶች ምርታቸውን ለዓለም እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ምቹ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

ኤክስፖው አምራቾችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ገዢዎች ጋር በቀጥታ እንደሚያገናኝም ተመላክቷል።

በማዕድና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች በኤክስፖው ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቃሉ።

የማዕድንና የቴክኖሎጂ ኤክስፖው እስከ ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም