የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ በማስመልከት የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ በማስመልከት የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፤ህዳር 12/2017(ኢዜአ)፦የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ በማስመልከት የተዘጋጀ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከፈተ።
በአውደ ርእዩ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ፣ የመዲናዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም ታዳሚዎች ተገኝተዋል።
አውደ ርዕዩ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እና የተገኙ ውጤቶች የቀረቡበት ሲሆን ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት፣የቤት ልማት ግንባታና እድሳት፣ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም፣ የውሃና ሌሎችም መሰረተ ልማቶችን የተመለከቱ ፎቶግራፎች ለእይታ ቀርበዋል።