ቀጥታ፡

ሁለተኛው የመላው አፍሪካ የጦር ኃይሎች የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2017 (ኢዜአ)፦ሁለተኛው የመላው አፍሪካ የጦር ኃይሎች የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በናይጄሪያ አቡጃ ተጀምሯል።

በፌስቲቫሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ25 የአፍሪካ አገራት የተወጣጡ 1 ሺህ 184 ስፖርተኞች ይሳተፋሉ።


 

ኢትዮጵያን የወከለው የመቻል ስፖርት ቡድን በአትሌቲክስ ውድድር ላይ ይሳተፋል።

የስፖርት ፌስቲቫሉ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ በአቡጃ ተካሄዷል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የቡድኑ መሪው እና የመቻል ስፖርት ክለብ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀነራል ኑሩ ሙዘይንና በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ገረመው እንዲሁም በኤምባሲው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ  ምስግና ተክሉ ተገኝተዋል።

የመቻል ስፓርትን ክለብ ወክለው በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የልዑካን ቡድን አባላትም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ በታዳሚው ፊት አልፈዋል።

በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚካሄደው የስፖርት ፌስቲቫል ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ከአገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም