ቀጥታ፡

ከጅቡቲ 104 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2017(ኢዜአ)፦መደበኛ ያልሆኑ 104 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው በሁለት ዙር እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ፍልሰተኞቹ የተመለሱት በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ትብብር መሆኑ ተገልጿል።

ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ በተጀመረው የክትትል ስራ በርካታ ኢትዮጵያውያን የህግ ከለላ እንዲያገኙ በማድረግ ከእንግልት እና ከሞት መታደግ መታደግ መቻሉን ኤምባሲው አመልክቷል።

ይህ ተግባር በሚቀጥሉት ጊዜያትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም