ቀጥታ፡

የኤሶል 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀመረ

ጅንካ፤ ህዳር 12/2017 (ኢዜአ)፦ በጂንካ ከተማ የሚገኘው የኤሶል 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሪ ዞን ከሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች በ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 50  ተማሪዎችን በመቀበል  የማስተማር ስራውን ጀመረ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው የመማር ማስተማር ስራውን በይፋ አስጀምረዋል።


 

የኤሶል 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ  ትምህርት ቤት በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች  በጋራ በመሆን የፈጠራ አቅማቸውን የሚያጎለብቱበትና በትምህርታቸው ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጻል

በትምህርት ቤቱ የተማሪዎች የመኝታ ክፍልን ጨምሮ የመመገቢያ አዳራሽና ካፍቴሪያ፣ ቤተ መፅሐፍት ፣ ምቹ የመማሪያ ክፍሎች ፣ ቤተ ሙከራዎችና የተማሪዎች የመዝናኛ ስፍራዎች እንዲሟሉ ተደርጓል፡፡

ትምህርት ቤቱ በዞኑ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የላቀ ውጤት ያላቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በመውሰድ የሚማሩበት የልህቀት ማዕከል እንደሆነም ተመላክታል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም