አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዝግጅትን ለመመልከት አርባምንጭ ከተማ ይገኛሉ - ኢዜአ አማርኛ
አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዝግጅትን ለመመልከት አርባምንጭ ከተማ ይገኛሉ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 12/2017(ኢዜአ)፦በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑካን ቡድን 19ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የዝግጅት ስራ ለመመልከት አርባምንጭ ከተማ ይገኛል።
አፈ ጉባኤው አርባምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የጋሞ አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት እንግዶችን ለመቀበልና በዓሉን ለማክበር እያደረገ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ይጠበቃል።
19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል"ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።