ቀጥታ፡

የመቻል ስፖርት ቡድን በመላው አፍሪካ የጦር ኃይሎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ይሳተፋል

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 11/2017(ኢዜአ)፦ የመቻል ስፖርት ቡድን በናይጄሪያ አቡጃ በሚካሄደው ሁለተኛው የመላው አፍሪካ የጦር ኃይሎች የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ አቡጃ ገብቷል።

ነገ የሚጀመረው ፌስቲቫል በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲሆን መቻል በአትሌቲክስ ውድድር ላይ ይሳተፋል።

በመቻል ስፖርት ክለብ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ኑሩ ሙዘይን የሚመራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አትሌቲክስ ቡድን ልምምዱን በአቡጃ እያደረገ ይገኛል።

በናይጀሪያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የጦር ኃይሎች ስፖርት ፌስቲቫል ነገ በሚደረግ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ይጀመራል።

የስፖርት ፌስቲቫሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በኬንያ አስተናጋጅነት ከተካሄደ በኋላ ለ20 ዓመታት ተቋርጦ ነበር።

ፌስቲቫሉ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ እንደሚካሄድ ከአገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም