የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2017(ኢዜአ)፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ።
ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።
የምክር ቤቱ አባላትም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።
በዚህም መሰረት የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 10/64/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።