ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መንግስት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአንኳን ደስ አለዎት መልእክት ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በሶማሊላንድ በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በመሆን በመመረጣቸው በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ስም የአንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፏል።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት እና ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ ላሳዩት ተምሳሌታዊነት ኢትዮጵያ አድናቆት እንዳላት የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ መጪው የሶማሊላንድ አስተዳደርም ስኬታማ ጊዜ እንዲገጥመው ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም