ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ባበረከተችው አስተዋፅኦ ለአለማችን ሃገሮች ምሳሌ ናት - ሌተናል ጄኔራል ምሃን ሰበርማኒያን

አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ባበረከተችው አስተዋፅኦ ለአለማችን ሃገሮች ምሳሌ ናት ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን የሰላም ማስከበር ሃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ምሃን ሰበርማኒያን ገለጹ።

አዛዡ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ግዳጁን በላቀ ብቃት የሚወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

የ18ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የሜዳሊያ ማልበስ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት ሌተናል ጄኔራል ምሃን ሰበርማኒያን ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ቀዳሚ ታሪክ ያላትና ከኮሪያ እስከ ደቡብ ሱዳን ባበረከተችው አስተዋፅኦም ለአለማችን ሃገሮች ምሳሌ እንደሆነች አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ጠንካራና የተሰጠውን ተልዕኮ በላቀ ብቃት እየተወጣ የሚገኝ መሆኑን የጠቆመት አዛዡ ሠራዊቱ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እያበረከተ የሚገኘው ሁለንተናዊ ድጋፍ ህዝባዊነቱን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰላም አሰከባሪ ሠራዊት ለደቡብ ሱዳን ህዝብ በሰላም ማስከበር ብቻ ሳይሆን በመሰረተ ልማቱም ዘርፈ ብዙ ድጋፎች ማድረጉን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም