ምክር ቤቱ በነገው መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ በነገው መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2017(ኢዜአ)፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
በስብሰባው ላይም የ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ አፈጻጸም ሪፖርትን ያዳምጣል።
እንዲሁም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።