ቀጥታ፡

አየር መንገዱ የ2025 የዓለም አራት ኮከብ አየር መንገድ ደረጃ እውቅና እና ሽልማት አገኘ

አዲስ አበባ፤ህዳር 9/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው አፔክስ የመንገደኞች ምርጫ የ2025 የዓለም አራት ኮከብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

የዓለም አራት ኮከብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጡ ድምፆች መሰረት የተበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።


 

ይህ ዕውቅና እና ሽልማት በዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑንም ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም