የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ምርታማነት ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይጫወታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ምርታማነት ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይጫወታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2017(ኢዜአ)፦ የሀገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ ምርታማነት ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ልማታችንን ከግብ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚመሩ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝቻለሁ ብለዋል።
ዕሴት በተጨመረበት ቡና ኤክስፖርት እና ብረታ ብረት ምርት ላይ የተካነው ኤኤምጂ ሆልዲንግስ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በመስተዋት እና በአሉሚኒየም ሥራዎች የሚታወቀው አንድነት መስተዋት ቴክኖሎጂ የግሉ ዘርፍ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽዖ ማሳያ ናቸው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል።