ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መንግስት በቀድሞው የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ህዳር 8/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መንግስት በቀድሞው የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሞሃመድ ሞሃመድ (ሲላንዮ) ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት አሕመድ፥ የኢትዮጵያ የረዠም ጊዜ ወዳጅ እንደነበሩ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ ሁለቱ ህዝቦች መካከልም ግንኙነትን በማጠናከር በኩል ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም