የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም አሶሳ ከተማ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም አሶሳ ከተማ ገቡ
አዲስ አበባ፤ህዳር 8/2017(ኢዜአ)፦የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና የሁሉም ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም ለመገምገም አሶሳ ከተማ ገብተዋል።
አመራሮቹ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ የፓርቲውን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ ሥራ አቅጣጫና መመሪያ ያስቀምጣሉ።
በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙም ተገልጻል።
አመራሮቹ አሶሳ ህዳሴ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድርና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።